የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ
ባህር ዳር ፤ ነሐሴ 19 ቀን 2015(ኢዜአ)፡-የአማራ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ያቀረቡትን የስራ መልቀቂያ ተቀብሎ በማፅደቅ በምትካቸው የአቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሾሟል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው አስቸኳይ ጉባኤ የክልሉን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
አቶ አረጋ ከበደ ባለፉት ጊዜያት የክልሉን ስራና ስልጠና ቢሮ ሲመሩ የቆዩ ሲሆን ከዚያ በፊትም በተለያዩ ተቋማት በሀላፊነት ሲሰሩ ቆይተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።