በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ የተሳተፉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ - ኢዜአ አማርኛ
በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች ማጣሪያ የተሳተፉት የኢትዮጵያ አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 19/2015 (ኢዜአ)፦ በሀንጋሪ ቡዳፔስት እየተካሄደ ባለው 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማምሻውን በተደረገው የ5 ሺህ ሜትር ወንዶች የማጣሪያ ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ፣ አትሌት በሪሁ አረጋዊና አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት ለፍጻሜ አልፈዋል።
የማጣሪያ ውድድሩ በሁለት ምድቦች ተከፍሎ የተከናወነ ሲሆን ከየምድቡ ከአንድ እስከ ስምንት የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
የፍጻሜ ውድድሩ እሁድ ነሐሴ 21/2015 ከምሽቱ 3 ሰዓት ከ10 ደቂቃ ላይ ይከናወናል።