በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የስማርት የወረዳ ማዕከልና የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ሕንጻዎች ተመረቁ - ኢዜአ አማርኛ
በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የስማርት የወረዳ ማዕከልና የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ሙያ ኮሌጅ ሕንጻዎች ተመረቁ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2015 (ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የተገነባው የስማርት የወረዳ ማዕከልና የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ሕንጻዎች ዛሬ ተመርቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማዕከሉና የኮሌጁ ሕንጻ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ ገልጸዋል።
ማዕከሉ የኢንፎርሜሽን ቴክሎጂ መሰረተ ልማት የተዘረጋለትና ለሰራተኞችና ለተገልጋዮች ምቹ ነው ያሉት ከንቲባዋ አገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋ ፣ፈጣንና ተደራሽ ለማድረግ እንደሚያግዝም አመልክተዋል።
በ2016 በጀት ዓመት ተጨማሪ 11 ስማርት የወረዳ ማዕከላት ግንባታ ስራ እንደሚጀመርም ጠቁመዋል።