ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2015(ኢዜአ፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ጎን ለጎን ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድ ራሞዲ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ላይም በተለይም ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ ቡድን ከመግባቷ ጋር ተያይዞ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልፀዋል።
ሁለቱ መሪዎች በፖለቲካዊ ትብብር ፣ በግብርና፣በቴክኖሎጂ፣ በንግድ እና በኢንቨስትመንት መስኮች የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጠናከር መስማማታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።