ቀጥታ፡

የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ ማጽደቁ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው--ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2015 (ኢዜአ) ፦ የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ ማጽደቁ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያ ሀገራችንን በአባልነት ተቀብሎ አፅድቁዋል፤ ይህ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ለሚሆን የበለፀገ የአለም ስርዓት መስፈን ከሁሉም ጋር ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናት ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል::

ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድኑ ጉበኤ ተቀባይት አግኝቷል።

15ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ እየተካሄደ ሲሆን በጉባኤው ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአዳዲስ አባልነት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም