ሁሉንም ያሳተፈና የበለጸገ የዓለም ስርዓት እንዲፈጠር ኢትየጵያ ከሁሉም ጋር ተባብራ ለመስራት ዝግጁ ናት-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

227

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ሁሉንም ያሳተፈና የበለጸገ የዓለም ስርዓት እንዲፈጠር ኢትዮጵያ ከሁሉም ጋር ተባብራ ለመስራት ዝግጁ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሪክስ አባል ሀገራት ኢትዮጵያ የቡድኑ አባል ለመሆን ያቀረበችውን ጥያቄ መቀበሉን ተከትሎ በቲውተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት በብሪክስ ቡድን መካተቱ ለኢትዮጵያ ታላቅ አጋጣሚ ነው ብለዋል።

የብሪክስ የመሪዎች ጉበኤ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ ከተማ እያካሄደ ባለው 15ኛው ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ አስተላልፏል።

የብሪክስ ቡድን በጉባኤው ኢትዮጵያ፣ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ አሳልፏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በቲውተር ገጹ ባስነበበው መልዕክት ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድኑ ጉበኤ ተቀባይት ማግኘቱን ጠቅሶ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም