ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ብሪክስን ተቀላቅለች

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 18/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ተቀላቅላች።

የብሪክስ የመሪዎች ጉበኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ አስተላለፈ።

15ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ ይገኛል።

ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳኡዲ አረቢያ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በአዳዲስ አባልነት ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ አስተላልፏል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በቲውተር ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ በደቡብ አፍሪካ ጁሃንስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የቡድኑ ጉበኤ ተቀባይት ማግኘቱን ጠቅሶ የእንኩዋን ደስ ያላችሁ መልእክቱን አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም