ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ከቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ከቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ ጋር ተወያዩ
አዲሰ አበባ፤ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ):-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ከሚካሄደው የBRICS-Africa Outreach እና BRICS Plus ስብሰባ በፊት ከቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በባለብዙ ወገን መድረኮች ላይ የበለጠ ትሥሥር ለመፍጠር ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግ ሀገራዊ ልማትን በመምራት ረገድ የጠቅላይ ሚኒስትሩን አመራር አድንቀው በሰላምና በልማት ጥረቶች፣ በመልሶ ግንባታው ዘርፍ እንዲሁም ኢንቨስትመንቶችን እና የንግድ ግንኙነቶችን በማጎልበት ረገድ መሻሻልን እንደሚደግፉ ቃል ገብተዋል።
ፕሬዝዳንት ሺ ጂንፒንግም በጋራ ማዕቀፍ ስምምነት መሰረት ቻይና ለኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2023/2024 ጊዜ ውስጥ ለደረሰ የዕዳ ክፍያ እፎይታ እንደምትሰጥ ጠቁመዋል።