መርማሪ ቦርዱ የጀመረውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ መቀጠል አለበት - ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶ - ኢዜአ አማርኛ
መርማሪ ቦርዱ የጀመረውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ መቀጠል አለበት - ምክትል አፈጉባኤ ሎሚ በዶ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ):-የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የጀመረውን ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ አስገነዘቡ።
መርማሪ ቦርዱ እስከ አሁን ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርትና የቀጣይ ስራዎች እቅድ ለምክር ቤቱ አቅርቧል።
ቦርዱ የተለያዩ ተጽዕኖዎች ሳይበግሩት ገለልተኛ ሆኖ እያከናወነ ላለው ተግባር ወይዘሮ ሎሚ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በቀጣይም የተፈጠረው አለመረጋጋት ተወግዶ የተሟላ ሰላም እንዲመጣ ክትትልና ቁጥጥሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ ቦርዱ “ገለልተኛ” ሆኖ ስራውን ለማከናወን እያደረጋቸው ላሉ ጥረቶች ምክር ቤቱ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በውይይቱም መርማሪ ቦርዱ በቀጣይ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በሚመለከት ዝርዝር እቅድና የመተዳደሪያ ደንብ ቀርቦ የተለያዩ የማስተካከያ አስተያየቶች ታክለውበት መፅደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።