ቀጥታ፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይናው ‘ቴቢያን ኤሌክትሪክ አፓራተስ’ ኩባንያ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 17/2015 (ኢዜአ):- በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይናው ‘ቴቢያን ኤሌክትሪክ አፓራተስ’ ኩባንያ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሹ ፌን ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

ውይይቱ ኩባንያው በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት በማስፋት በአዲስ የኃይል አማራጮች እና ማዕድን ዘርፎች መሰማራት በሚችልበት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

አምባሳደር ተፈራ ኩባንያው በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎች አስመልክቶ ማድረጋቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

‘ቴቢያን ኤሌክትሪክ አፓራተስ’ ኩባንያ የኃይል ትራንስፎርመሮችና የተለያዩ የኤሌክትሪክ መሳሪዎችን ያመርታል።

ኩባንያው በቻይና ከሚገኙ ግዙፍ የትራስፎርመር አምራቾች መካከል የሚጠቀስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም