የተርኪዬው ‘ኤች ኤስ ኦ’ ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳየ - ኢዜአ አማርኛ
የተርኪዬው ‘ኤች ኤስ ኦ’ ኩባንያ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎቱን አሳየ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ)፦የተርኪዬ የጫማ ግብአቶች ዘርፍ አምራች የሆነው ‘ኤች ኤስ ኦ’ ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር ከኩባንያው ባለቤት ሃካን ጉችሉ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር አደም በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ገለጻ አድርገዋል።
ኩባንያው በኢትዮጵያ የጫማ ግብአቶች በማምረት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ሃካን ጉችሉ ገልጸዋል።
በቀጣይ ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት እቅድ እንደያዙ መናገራቸውን ኢዜአ አንካራ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
‘ኤች ኤስ ኦ’ ኩባንያ በተርኪዬ የተለያዩ ከተሞችና በኡዝቤክስታን የጫማ ግብአት አምራች ኩባንያዎች አሉት።