ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጆሃንስበርግ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጆሃንስበርግ ገቡ
አዲስ አበባ ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካቸው ዛሬ በሚጀመረው የብሪክስ-አፍሪካ እና ብሪክስ ፕላስ መርሐ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡