ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጆሃንስበርግ ገቡ

አዲስ አበባ ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ከሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ጋር በመሆን ደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ገብተዋል።
 

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ልዑካቸው ዛሬ በሚጀመረው የብሪክስ-አፍሪካ እና ብሪክስ ፕላስ መርሐ ግብር ላይ እንደሚሳተፉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም