ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ዳግም እንዲጀመር የጋራ ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ ገለጹ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 17/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ መንግስትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቡድን በአስቸጋሪ ሁኔታ ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ዳግም በፍጥነት እንዲጀመር የጋራ ጥረቶቻቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታወቁ።

መንግስት ከወቅቱ የተመድ የኢትዮጵያ ተወካይና የሰብአዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ዶክተር ራሚዝ አላክባሮቭና የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት(ኦቻ) የኢትዮጵያ ተወካይ ሚሼል ሳድን ጨምሮ ከሌሎች የድርጅቱ የኢትዮጵያ ቡድን ተወካዮች ጋር ገንቢና ፍሬያማ ውይይት ማድረጉ ተገልጿል።

ከውይይቱ በኋላ መንግስትና የተመድ የኢትዮጵያ ቡድን ባወጡት የጋራ መግለጫ ሁለቱ ወገኖች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንዲሁም በኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማት ለማምጣት በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የሰብዓዊ እርዳታ በአፋጣኝ በድጋሚ እንዲጀመር የጋራ ጥረታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማመልከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም