ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን  በውድድር እንደሚቀበል ገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 16/2015 (ኢዜአ):- የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ2016 የትምህርት ዘመን ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን  በውድድር እንደሚቀበል ገለጸ።

ዩኒቨርሲቲው  በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ መሰረት የመጀመሪያው የመንግስት ራስ ገዝ አስተዳደር ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ይታወቃል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የራስ ገዝ አስተዳደር ውሳኔው የትምህርት ጥራትን በማሻሻል ብቁ የሰው ሀይል ለማፍራት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና የአስተዳደር ሙሉ ነፃነት ኖሮት በሃላፊነት እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት።

በዚህም ከ2016 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በትምህርት ሚኒስቴር የመቁረጫ ነጥብ ያገኙ የቅድመ ምርቃ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበልም ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነትን ሙሉ ለሙሉ ለመተግበር የሚያስችሉ ከአስተዳደር መመሪያዎች ዝግጅት ጀምሮ የተለያዩ ሰነዶችን ማዘጋጀቱንም ተናግረዋል።

በተጨማሪም የጥናትና ምርምር ስራውን ለማሳለጥ የሚያግዙ የፋይናንስ፣ የሰው ሀይል አስተዳደር እና የግዥ መመሪያዎች እንደሚሻሻሉም አስታውቀዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም