ቀጥታ፡

ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ሲሞክሩ ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ስለ ተባሉ ዜጎች መንግስት ጉዳዩን እየተከታተለ ነው - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 16/2015 (ኢዜአ):-መንግስት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ለመሻገር ሲሞክሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ- የመን ድንበር ላይ “በጅምላ ተገድለዋል” በሚል ሂውማን ራይትስ ዎች የተባለ ተቋም በቅርቡ ባወጣው ዘገባ ላይ የተላለፈውን መረጃ በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ መንግስት ጋር በመሆን ጉዳዩን በአስቸኳይ በማጣራት የሚያሳውቅ ሲሆን ምርመራው እስኪጠናቀቅ ድረስ አላስፈላጊ ግምቶችን ከማድረግ መቆጠብ እንደሚገባ ገልጿል።

ኢትዮጵያና ሳዑዲ አረብያ የረዥም ጊዜ ጠንካራና ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዳላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም