የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
ድሬዳዋ፣ ነሐሴ 16/2015 (ኢዜአ)፡- የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት 3ተኛ የሥራ ዘመን 2ተኛ ዓመት ሁለተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በመድረኩ ለውይይት የሚሆን መነሻ ጽሁፍ አቅርበዋል።
በዚህም ለሀገር ዘላቂ ሰላም እና ልማት መንግስት የተቀናጀ ሥራ እያከናወነ መሆኑን ነው የገለጹት።
የመንግስት ሁሉን አቀፍ ጥረቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ በየደረጃው ያሉ የምክር ቤት አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሰላም እና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ በሚከናወኑ ተግባራት ውስጥ የምክር ቤቱ አባላት ከመቼውም ጊዜ በላይ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ነው አቶ ኢብራሂም የተናገሩት።
በአገር ደረጃ የተጀመረውን ሁሉን አቀፍ የሰላም፣ የልማት እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የምክር ቤቱ አባላት የድርሻቸውን እንደሚወጡ አመልክተዋል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በአስቸኳይ ጉባኤው ከወቅታዊ ጉዳይ ውይይት ባለፈ የተለያዩ ሹመቶችን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።