ቀጥታ፡

የሕንዱ ሲልቨር ስፓርክ አፓረል ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋት ፍላጎት አለው

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15/2015(ኢዜአ):-የሕንዱ ሲልቨር ስፓርክ አፓረል ኩባንያ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ እና ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ከኩባንያው  ባለቤት እና የማኔጅመንት ቡድን  ጋር ተወያይቷል።

ኮሚሽነር ለሊሴ ኩባንያው በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እያደረገ ያለውን የኢንቨስትመን አድንቀዋል።

መንግስት ለኩባንያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንኛ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እንድትሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል።


 

የሕንዱ ሲልቨር ስፓርክ አፓረል ኩባንያ አመራሮች በበኩላቸው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እያደረገላቸው ላለው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኩባንያው በቀጣይ በኢትዮጵያ ያለውን ኢንቨስትመንት ለማስፋት ያለውን እቅድም ጠቅሰዋል።

የሕንዱ ሲልቨር ስፓርክ አፓረል ኩባንያ ለ2 ሺህ 600 ኢትዮጵያውያን የስራ እድል መፍጠሩንና ምርቶቹን ለአሜሪካ እየላከ እንደሚገኝ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም