የኢትዮጵያን ስም በላባቸው ከፍ ያደረጉ ጀግኖች አትሌቶች ምስጋና ይገባቸዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያን ስም በላባቸው ከፍ ያደረጉ ጀግኖች አትሌቶች ምስጋና ይገባቸዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2015(ኢዜአ):-የኢትዮጵያን ስም በዓለም አደባባይ በላባቸው ከፍ ያደረጉ ጀግኖች አትሌቶች ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባዋ በማህብራዊ ትስስር ገጻቸው "እንኳን ደስ አለን! በላባችሁ የኢትዮጵያን ስም በወርቅ ፃፋችሁ ! ሲሉ አስፍረዋል።
ትላንት ምሽት በተካሄደው በ19ኛው የቡዳፔስት የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና መክፈቻ ላይ በተደረገው የሴቶች የ10 ሺ ሜትር ሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ፦
1.ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ
2. ለተሰንበት ግደይ ብር
3.እጅጋየሁ ታዬ ነሃስ
በማምጣት ባስመዘገቡት አኩሪ ድል የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው "በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!" ብለዋል ከንቲባዋ።