ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ላስጠሩ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ላስጠሩ አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፉ
አዲሰ አበባ፤ነሐሴ 14/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቡዳፔስት የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ10,000 ሜትር ውድድር ላይ ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ ላይረጉ አትሌቶች የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ትላንት ምሽት በተካሄደው በ19ኛው የቡዳፔስት የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና መክፈቻ ላይ በተደረገው የሴቶች የ10 ሺ ሜትር ሩጫ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች ፦
1.ጉዳፍ ፀጋይ ወርቅ
2. ለተሰንበት ግደይ ብር
3.እጅጋየሁ ታዬ ነሃስ
በማምጣት አኩሪ ድል ማስመዝገባቸው ይታወቃል።