በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብዙ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች እነማን ናቸው? - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብዙ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶች እነማን ናቸው?
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 13/2015 (ኢዜአ) ፡- በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ብዙ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለኢትዮጵያ ያስገኙ አትሌቶችን እናስታውሳችሁ።
19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ በሀንጋሪ ቡዳፔስት ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ 18 ሻምፒዮናዎች እ.አ.አ በ1987 በጣልያን ሮም ከተከናወነው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በስተቀር በ17ቱ ላይ ተሳትፋለች።
ኢትዮጵያ እስከ አሁን በተካፈለችባቸው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 33 የወርቅ፣ 34 የብር እና 28 የነሀስ በድምሩ 95 ሜዳሊያዎችን በማግኘት በሻምፒዮናው የምንጊዜም የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
33ቱ የወርቅ ሜዳሊያዎች የተገኙት በ19 አትሌቶች ነው።
በሻምፒዮናዎቹ ብዙ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኙ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ዝርዝር ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል።
1. አትሌት ቀነኒሳ በቀለ 5 የወርቅ ሜዳሊያዎች
2. አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 5 የወርቅ ሜዳሊያዎች
3. ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ 4 የወርቅ ሜዳሊያዎች
4. አትሌት መሰረት ደፋር 2 የወርቅ ሜዳሊያዎች
5. አትሌት አልማዝ አያና 2 የወርቅ ሜዳሊያዎች እንዲሁም
6. አትሌት ሙክታር እድሪስ በተመሳሳይ 2 የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝተዋል።