ቀጥታ፡

የ"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" ምክር ቤት ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎን ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ

ሆሳዕና ፣ነሀሴ 13:2015 ( ኢዜአ ) :- አዲስ የተደራጀው የ"ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል" ምክር ቤት ወይዘሮ ፋጤ ሰርሞሎን የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ አድርጎ መረጠ።

የክልሉን ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በመወከል እጩዋን ያቀረቡት አቶ ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል፣ ወይዘሮ ፋጤ ሱርሞሎ በነባሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በተለያዩ የስራ ኃላፊነት ሲያገለግሉ የቆዩ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ምክር ቤቱ በፓርቲው የቀረቡት እጩ ካላቸው የስራ ልምድና የሚሰጣቸውን የስራ ኃላፊነት ለመወጣት ያላቸውን ተነሳሽነት ጨምሮ በቀረበው ዝርዝር ሀሳብ ላይ በመወያየት የዋና አፈ ጉባዋን መርጧል።


 

እንዲሁም የቀድሞ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል ምክር ቤት የህግ፣ ፍትህና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበሩት ወይዘሮ መነቴ መንዲኖን ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።

ተሻሚዎችም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም