ቀጥታ፡

የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ሽልማት ሰጠ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 12/2015 (ኢዜአ)፡-የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የ"ፕላኪው ኦፍ ሜሪት" ሽልማት አበርክቷል።

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ሽልማቱን ከዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ከሰባስቲያን ኮ ተቀብላለች።

ደራርቱ ሽልማቱ የተበረከተላት በዓለም አትሌቲክስ እና በአትሌቲክስ ስፖርት ላበረከተችው አስተዋጽኦ መሆኑን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሀንጋሪ ቡዳፔስት ሲካሄድ የቆየው 54ኛው የዓለም አትሌቲክስ ኮንግረስ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ዛሬ ተጠናቋል።

ኮንግረሱ 55ኛው ስብስባ እ.አ.አ በ2025 በጃፓን እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም