የማዕከላዊ ኢትዮጵያና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
ሆሳዕና ፤ ነሀሴ 12/2015( ኢዜአ)፡- የማዕከላዊ ኢትዮጵያና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ በወልቂጤና አርባ ምንጭ ከተሞች እየተካሄደ ነው።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታውን እያካሄደ ያለው ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ካምባታ ጣምባሮ፣ ሃላባ፣ ሀዲያ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳን በማካተት መሆኑ ይታወቃል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የነባሩን ክልል ህገ መንግስት ለማሻሻል በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።
በመርሐ ግብሩ የፌዴራል፣ የአምስቱም ዞኖችና የልዩ ወረዳው አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።
በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ አካል የሆነው የክልሉ ረቂቅ ህገ-መንግስት ላይ ያተኮረ ውይይት በአርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በጉባኤው የክልል አደረጃጀት ሂደት በተመለከተ የክልሉ አደረጃጀት የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በኩል ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደርግበታል ተብሏል።
ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ6 ማዕከላት የተዋቀረ ሲሆን ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ ሳውላና ካራት ናቸው።
የምስረታ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች አካትቶ የሚደራጅ ነው።