ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት... የአገሪቱ ፕሬዝዳንት - ኢዜአ አማርኛ
ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት አላት... የአገሪቱ ፕሬዝዳንት
አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 10/20215 (ኢዜአ):-ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላት የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርቆስ ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ በፊሊፒንስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙትን ደሴ ዳልኬን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም ፊሊፒንስ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራች ነው፡፡
ፕሬዝዳንቱ ሃገራቸው የተሻለ ተስፋ ካላት አፍሪካ በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ልውውጥና በሌሎች ዘርፎች ይበልጥ ተቀራርቦ የመስራት ፍላጎት እንዳላት ባብራሩበት ንግግራቸው “ኢትየጵያ አፍሪካ እያሳየች ባለችው ምጣኔሃብታዊ ለውጥ አለም እየተደመመ” መሆኑን አብራርተዋል።
በፊሊፒንስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ደሴ ዳልኬ በበኩላቸው “ፊሊፒንስ ግብርናዋን ከተለምዶ አሰራር በማውጣት ዘመናዊ ማድረግ ቀጥሎም ወደ አገልግሎትና የማምረቻ ዘርፍ የተሸጋገረችበት ተሞክሮ የፊሊፒንስ ባለሙያዎች የቴክኖሎጂ አቀባበልና የስራ ትጋት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ሃገራቸው ኢትዮጵያም የመዋቅር ለውጥ በማድረግ በሂደት ወደ ማምረቻ ዘርፉ በመግባት በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ኤኮኖሚ እየገነባች መሆኑን መግለጻቸውን ጂ ኤም ኤን ኔት ዎርክ የተባለው ድረ ገጽ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ እድገቷን ለማስቀጠል ከፊሊፒንስ የምትወስዳቸው በርካታ መልካም ተሞክሮዎች መኖራቸውን ድረ ገጹ አስነብቦል።
ኢትዮጵያና ፊሊፒንስ መደበኛ የሚባለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1977 ነበር።