በ2015 በጀት ዓመት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶችና የመድሀኒት ግብአቶች አስፈላጊውን የጥራት መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉ ተገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በ2015 በጀት ዓመት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶችና የመድሀኒት ግብአቶች አስፈላጊውን የጥራት መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 9/2015 (ኢዜአ) ፡- በተጠናቀቀው 2015 በጀት ዓመት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶች እና የመድሀኒት ግብአቶች አስፈላጊውን የጥራት መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉ ተገለጸ።
የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ አበራ ደነቀ ጉዳዩን አስመልክተው ለመገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥተዋል።
በእዚህም በ2015 በጀት ዓመት ከ42 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ መድሀኒቶች እና የመድሀኒት ግብአቶች አስፈላጊውን የጥራት መስፈርት ባለማሟላታቸው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ መደረጉን ገልጸዋል።
በተጨማሪም ከ33 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውና በጉዞ ወቅት የተበላሹ እና የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የህክምና መሳሪያዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ መደረጉንም አስታውቀዋል።
በበጀት ዓመቱ ከ13 ሺህ ቶን በላይ የሚመዝኑ አና ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የምግብ ምርቶች በጉዞ ወቅት በመበላሸታቸው ወደ ሀገር ውሰጥ ገብተው ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ተደርገዋል ብለዋል።