ቀጥታ፡

በ2015 ዓ.ም ሶስት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ አገር ቤት መመለሳቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 9/2015(ኢዜአ)፡- በ2015 ዓ.ም ሶስት ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ከጅቡቲ ወደ አገር ቤት መመለስ መቻሉን በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ።

ኤምባሲው ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት(አይኦኤም) ጋር በመተባበር ዜጎች ሰብአዊ ክብራቸው ተጠብቆ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ በማመቻቸት ረገድ ሰፊ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።


 

በ2015 ዓ.ም ብቻ 2 ሺህ 966 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን በጅቡቲ ወደ አገር ቤት መመለስ መቻሉን አመልክቷል።

ችግሩን ከምንጩ ለመፍታትም ከሚመለከታቸው የኢትዮጵያና የጅቡቲ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ መሆኑንም ነው ኤምባሲው ያስታወቀው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም