የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በ2016 አገራዊ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽነሮች በ2016 አገራዊ የፀጥታ ዕቅድ ላይ ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 8/2015 (ኢዜአ) ፡- የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽነሮች በ2016 በጀት ዓመት አገራዊ የፀጥታ እቅድ ላይ ተወያይተዋል።
ኮሚሽነሮቹ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና አገራዊ ነባራዊ ሁኔታን ተንትኖ በተዘጋጀው የፀጥታ እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያመላክታል።
እቅዱም የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያሰራ መሆኑም ተገልጿል።
የፌዴራል፣ የክልልና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የፖሊስ ኮሚሽነሮቹ ባዘጋጁት እቅድ እየተመሩ ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ መግለጻቸውም ተመላክቷል።