ቀጥታ፡

ኢትዮጵያን በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚወክሉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 7/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያን በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚወክሉ አትሌቶች ሽኝት ተደረገላቸው።

19ኛው የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከነሐሴ 13 እስከ 21 ቀን 2015 ዓ.ም በሀንጋሪ ቡዳፔስት ከተማ ይካሄዳል።

በዚህ ሻምፒዮና ከ200 ሀገራት የተውጣጡ 2 ሺህ ያህል አትሌቶች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሚጀመረው በዚህ ውድድር ኢትዮጵያም ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ርቀቶች የምትሳተፍ ይሆናል።

ኢትዮጵያም በዚህ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ19 ሴት እና በ16 ወንድ በድምሩ በ35 አትሌቶች ትወከላለች።

በሻምፒዮናው የሚሳተፉ አትሌቶች በዛሬው እለት ሽኝት ተደርጎላቸዋል።

በሽኝት መርሃ-ግብሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ የተለያዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም