የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ጉዞውን በድል ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የማጣሪያ ጉዞውን በድል ጀመረ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2015(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሴቶች ክለብ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን የመጀመሪያ ጨዋታ የብሩንዲውን ቡጃ ኩዊንስ 2 ለ 1 አሸንፏል።
በንጄሩ ከተማ ‘FUFA Technical Center Stadium’ በተደረገው ጨዋታ አረጋሽ ካልሳ እና ሎዛ አበራ ለንግድ ባንክ የማሸነፊያ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ቶፒስተር ሲቱማ ለቡጃ ኩዊንስ ብቸኛውን ግብ አስቆጥራለች።
በምድብ አንድ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ ጨዋታውን ከጅቡቲው ፋድ ክለብ ጋር ነሐሴ 9/2015 ያከናውናል።