የቡሌ ሆራ ከተማ የተመሰረተችበትን 100ኛ ዓመት እያከበረች ነው - ኢዜአ አማርኛ
የቡሌ ሆራ ከተማ የተመሰረተችበትን 100ኛ ዓመት እያከበረች ነው
ቡሌ ሆራ ፤ ነሐሴ 6 /2015(ኢዜአ)፡- የቡሌ ሆራ ከተማ የተመሰረተችበትን 100ኛ ዓመት በዓል የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት በተገኙበት እያከበረች ነው።
ከተማዋ የምስረታ በዓሏን ከመካከለኛ ወደ ከፍተኛ የከተማ ደረጃ ሽግግርን መረሃ ግብርን በማካተት ጭምር እያከበረች ትገኛለች።
በህብረተሰቡ ተሳትፎ የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድንና ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤትን ጨምሮ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት እንደሚበቁም ይጠበቃል።
በበዓሉ ላይ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አወሉ አብዲና የብልጽግና ፓርቲ የክልሉ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ናማራ ቡሊን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራል ፣የክልልና የዞን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ታድመዋል።
ከቦረናና ከጌዴኦ ዞኖች እንዲሁም ከሲዳማና ሌሎች አጎራባች አካባቢዎች የተጋበዙ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎችና የህብረተሰቡ ተወካዮች ተገኝተዋል።
በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ከተማ የሆነችው ቡሌ ሆራ በ7 ቀበሌዎች የተዋቀረች ስትሆን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝባት ናት።