ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች እያስመረቀ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች እያስመረቀ ነው
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2015 (ኢዜአ)፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት የብላቴ ኮማንዶ እና የአየር ወለድ ማሰልጠኛ ማዕከል ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በማስመረቅ ላይ ነው።
ተመራቂዎቹ የተለያዩ አስቸጋሪ መሰናክሎችን ማለፍን እንዲሁም ፈጥኖ መድረስን ለሚጠይቁ ተልእኮዎች ጠንካራ ስልጠና የወሰዱ መሆናቸው ተመላክቷል።
የምርቃት በዓሉን በማስመልከት ሰልጣኞቹ ያገኙትን ክህሎት በትልቅ የአምሳለ-እውን ትርኢት ማሳያታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።
በመርሐ-ግብሩ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሺዎች የሚቆጠሩ ታዳሚዎችን የማስተናገድ አቅም ኖሮት በማሰልጠኛ ማዕከሉ የተገነባውን አምፊ ቲያትር በይፋ የከፈቱ ሲሆን በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ችግኞችን ተክለዋል።