ቀጥታ፡

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዩጋንዳ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2015(ኢዜአ)፡- ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በዩጋንዳ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ካምፓላ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተደረገው ውይይት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።


 

በውይይቱ ላይ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እፀገነት በዛብህና ሌሎች የሚሲዮኑ አባላት ተገኝተዋል።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በያዝነው ሳምንት በዩጋንዳ ካምፓላ በተካሄደው ሁለተኛው ጂ-25 የአፍሪካ ቡና ጉባኤ ላይ መሳተፋቸው በካምፓላ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መግለጹ ይታወሳል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም