ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 5/2015(ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታን ዛሬ ጠዋት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ቀጥሎ ባለው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን የማጠናከር ስራ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሩዋንዳ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ቪንሴንት ቢሩታን ዛሬ ጠዋት በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸው ተገልጿል።
ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በ1970ዎቹ መገባደጃ ላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ በኋላ ጠንካራ እና ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ የሁለትዮሽ ትብብር ፈጥረዋል።
በዚህ ጊዜ ውስጥም በርካታ የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነቶች በተለያዩ ዘርፎች ተፈራርመዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ከውይይታቸውም ቀጥሎ ችግኞችን በአንድነት ፓርክ መትከላቸው ተገልጿል።