ኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የግብርና ተቋም ፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር መከሩ - ኢዜአ አማርኛ
ኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የግብርና ተቋም ፋኦ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር መከሩ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 4/2015 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ እና የግብርና ተቋም ፋኦ (FAO) የኢትዮጵያ ተወካይ ከሆኑት ፍራይ ዚሙድዚ ጋር መክረዋል።
ምክክራቸውም ሁለቱ ተቋማት በተለይም በግብርናው ዘርፍ በጋራ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን መሳብ በሚቻሉባቸው ስትራቴጂካዊ መንገዶች ዙሪያ ላይ ያተኮረ እንደነበር ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።