ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ አከናውናለች-የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 4/2015 (ኢዜአ) ፦ ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ መከወኗን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፤ በውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ባለፈው ሳምንት የባለብዙ ወገንና የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ እንደጎለበተ ማሳያ የሆኑ ጉብኝቶች መደረጋቸውን ገልጸዋል።

በዚህም ባለፈው ሳምንት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት፣ የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ናሌዲ ፓንዶር፣ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዮሺማሳ ሃያሺ እና የደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጋቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በተጨማሪም የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝትም የዚሁ የውጤታማ ዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህ ጉብኝቶች በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ያለውን ትብብር የበለጠ እንዲጠናከር ለማድረግ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ የተሰራበት ሳምንት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ ባለፈው ሳምንት በባለብዙ ወገንና በሁለትዮሽ ግንኙነት ውጤታማ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ማከናወኗን ጠቅሰዋል።

ይህ ውጤታማ የዲፕሎማሲ ስራ በ2016 በጀት ዓመትም የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም