በተያዘው በጀት ዓመት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት የሕብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ይገባል- ዶክተር አለሙ ስሜ - ኢዜአ አማርኛ
በተያዘው በጀት ዓመት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት የሕብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ ይገባል- ዶክተር አለሙ ስሜ
ጅግጅጋ ፤ ነሐሴ 2/2015 (ኢዜአ)፦ በ2016 በጀት ዓመት በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት የሕብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ ገለጹ።
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴርና የክልል ተጠሪ ተቋማት አመራሮች ተቋማዊ የእቅድ ግምገማ ዛሬ በጅግጅጋ ከተማ ተጀምሯል።
በግምገማው ላይ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ፣ የክልሎች ሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች እና የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በዘርፉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተከናወኑ ስራዎችን በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ ማከናወን በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር መድረኩ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በፌዴራልና በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ተቋማት የተቀመጡ እቅዶች ቀርበው እንደሚገመገሙም አመልክተዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት በኢትዮጵያ ቀልጣፋ እና ዘመናዊ አገልግሎትን በማሳለጥ የሕብረተሰቡን እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።