የኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 2/2015 (ኢዜአ)፦ የኮሪያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓርክ ጂን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፓርክ ጂን በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ይወያያሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ እና ኮሪያ ሪፐብሊክ ከ70 ዓመት በላይ የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላቸው።