የተርኪዬ አልፋ ግሩፕ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
የተርኪዬ አልፋ ግሩፕ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 1/2015(ኢዜአ)፦ በኢነርጂ ዘርፍ ላይ የሚሰራው የተርኪዬ አልፋ ግሩፕ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው አስታወቀ።
በተርኪዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ ከኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ አህመት ሙራት ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ያተኮረ ሲሆን በዘርፉ ያሉ እድሎችን አስመልክቶ ገለጻ ተደርጓል።
የኩባንያው ባለሀብቶች በበኩላቸው በኢትዮጵያ በኢነርጂው ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው እና በቀጣይ ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ መግለጻቸውን በአንካራ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
አልፋ ግሩፕ እ.አ.አ 1999 የተቋቋመ ኩባንያ ነው።