ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ተወያየ 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 28/2015 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የፓለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ጋር ተወያየ  ።

”የውይይቱ ዓላማ ኮሚሽኑ በጋራ ምክር ቤቱ አጋዥነት በሠራቸው ሥራዎች ላይ ገለፃ ለመስጠት እና በቀጣይ ሥራዎቹ ላይ ውይይቶችን ለማድረግ ነው። 

በውይይት መድረኩ ላይ ኮሚሽኑ ተሳታፊዎችን ለመለየት በተንቀሳቀሰባቸው የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የፖሊቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤቱ እገዛን እንዳደረገለት ተገልጿል። 

ከውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች እና ገንቢ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ በተሳታፊዎች ልየታ ሂደት እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ሊያስተካክላቸው ስለሚገባቸው ነገሮች ሀሳቦች እና አስተያየቶች መቅረባቸው ተመላክቷል። 


 

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደጠቀሱት ሁሉም በትጥቅ ትግል ወይም በሰላማዊ መንገድ ተሰልፈው ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች የሀገራዊ ምክክሩ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። 

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ባቀረባቸው መሰል ጥሪዎች ምላሽ በመስጠት በዝግጅቱ ላይ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) ተወካዮች ፓርቲውን ወክለው የተገኙ ሲሆን፣ ከኮሚሽኑ ጋር በጋራ ለመስራት ያላቸውን ፈቃደኝነትም መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም