የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አተረፈ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር አተረፈ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 27/2015 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2015 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ።
የባንኩ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዮሐንስ አያሌው የበጀት ዓመቱን አፈጻጸም በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፤ ባለፉት የለውጥ ዓመታት በተወሰዱ የማሻሻያ እርምጃዎች ባንኩ ከኪሳራ ወጥቶ ውጤታማ ወደ መሆን እየተሸጋገረ ነው ብለዋል።
ለአብነትም ባንኩ የተበላሸ ብድር በማስተካከል ጤናማ መሆን እንዲችል የሚያስችሉ የለውጥ ሥራዎች ውጤት እያመጡ መሆኑን በማንሳት።
በዚህም የባንኩ የተበላሸ ብድር መጠን ከለውጡ በፊት 43 በመቶ እንደነበር በማንሳት፤ በ2015 ወደ 7 ነጥብ 1 በመቶ ማውረድ ተችሏል ብለዋል።
ባንኩ በ2015 በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልጸው በዚህም ከታክስ በፊት 6 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝቷል ብለዋል።
ባንኩ ባለፉት 3 ዓመታት 15 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ማትረፉን ጠቁመው፤ ባንኩ ገብቶበት ከነበረበት ኪሳራ ወጥቶ እዚህ ውጤት ላይ መድረሱ ትልቅ ስኬት መሆኑንም አብራርተዋል።
የባንኩ ካፒታል አሁን ላይ 38 ቢሊዮን ብር መድረሱንም ገልፀዋል።