“መደመር ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
“መደመር ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 27/2015 (ኢዜአ) :- “መደመር ለህብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ሀሳብ ሀገር አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ባዘጋጀው በዚህ የውይይት መድረክ ላይ በመደመር እሳቤዎች ዙሪያ ያተኮሩ አራት ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።
በውይይቱ የመደመር እሳቤ ለሰላም፣ ለልማት እንዲሁም ለብልጽግና መረጋገጥ ያለው ሚና ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ተጠቁሟል።
በሌላ መልኩ ብሔራዊ መግባባት መፍጠር በሚያስችሉ ሃሳቦች ዙሪያ ውይይት እንደሚካሄድ ተገልጿል።
በመድረኩ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።