የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 27/2015 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል።
በመርሀ ግብሩ የጉባኤው የበላይ ጠባቂ አባቶች እና የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
ጉባኤው በዛሬው እለት የ2015 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም እና የ2016 በጀት አመት እቅድ ላይ ይወያያል።
እንዲሁም የስራና የሂሳብ ሪፖርት እና አመታዊ ረቂቅ እቅድ ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።