ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ - ኢዜአ አማርኛ
ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 26 /2015(ኢዜአ)፡- ለሸኔ የሽብር ቡድን የትጥቅ ድጋፍ አድርገዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በአዋሽ አርባ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
የፖሊስ ምርመራ ቡድን ከፍርድ ቤት የብርበራና የፍተሻ ትዕዛዝ በማውጣት በተጠርጣሪዎቹ መኖሪያ ቤት ፍተሻ በማድረግ አዋሽ አርባ ከሚገኘው የሾፌሩ መኖሪያ ቤት 750 የክላሺንኮቭ እና የብሬን ጥይቶችን ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አመልክቷል።
ፌደራል ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ እያካሄደ ያለውን ምርመራ አጠናክሮ መቀጠሉንና ሕብረተሰቡ መሰል የወንጀል ተግባራትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት በፍጥነት ጥቆማ በመስጠት ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።