አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከዓለም አቀፉ የሶላር ጥምረት ዳይሬክተር ጀነራል ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከዓለም አቀፉ የሶላር ጥምረት ዳይሬክተር ጀነራል ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 26/2015 (ኢዜአ)፡- በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ከዓለም አቀፉ የሶላር ጥምረት ዳይሬክተር ጀነራል ዶክተር አጃይ ማቱር ጋር ተወያዩ።
ውይይታቸውም በኢትዮጵያ እና ድርጅቱ መካከል በሶላር ኢነርጂ ፕሮግራም ያለውን ትብብር የበለጠ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
ዶክተር አጃይ በድርጅታቸው እና በኢትዮጵያ መካከል በሶስት ጉዳዮች ላይ የተደረሱት ሶስት ስምምነቶች ትግበራ ያሉበትን ደረጃ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የሶላር ጥምረት በሶላራይዜሽን ፕሮግራም አማካኝነት ለመስኖ እና ለመጠጥ አገልግሎት የሚሆኑ የውሃ መሳቢያ ፓምፕ አቅርቦት እንዲሁም የሶላር ቴክኖሎጂ መተግበሪያ ማዕከል ግንባታ ላይ የጋራ ስምምንት እንዳላቸው አስታውሰዋል።
አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ድርጅቱ ከኢትዮጵያ ጋር በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ ስኬታማ ስራ እንድትሰራ በሶላር ፓርክ እና በሶላር ፓምፕ ዙሪያ በትብብር ለመስራት ያሳየውን ቁርጠኝነት አመስግነዋል።