ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ከጉያና ጋር ትጫወታለች

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 26/2015 (ኢዜአ) :- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከጉያና አቻው ጋር በአሜሪካ ዛሬ የወዳጅነት ጨዋታውን ያደርጋል።

ብሔራዊ ቡድኑ የወዳጅነት ጨዋታዎች ለማድረግ ከትናንት በስቲያ አሜሪካ መግባቱ ይታወቃል።

በጊዜያዊ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ዳንኤል ገብረማርያም የሚመራው ቡድን ማረፊያውን በቨርጂኒያ ግዛት አድርጓል።

ዋልያዎቹ የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ዛሬ ከሌሊቱ 8 ሰአት ላይ በሴግራ ፊልድ ስታዲየም ከጉያና ብሔራዊ ቡድን ጋር ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ብሔራዊ ቡድኑ የዛሬውን ግጥሚያ በሚያደርግበት ስታዲየም ትላንት ልምምድ ያደረገ ሲሆን ይህ ጨዋታ በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር(ፊፋ) መመዝገቡን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

ቡድኑ ሁለተኛ ጨዋታውን ሐምሌ 29 ከአትላንታ ሮቨርስ ጋር ጨዋታውን ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም