ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አመራሮች ቅንጅታዊ አሰራርን ማጎልበት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

 

አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 26/2015 (ኢዜአ) ፡- የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አመራሮች የሁለቱን ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ማጎልበት በሚቻልባቸው ስትራቴጂያዊ መንገዶች ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

የሁለቱ ተቋማት አመራሮች በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፕሮሞሽን፣ በድጋፍ እና ክትትል በኩል አብሮ ለመስራት የታቀዱ የጋራ ዕቅዶች ላይ ምክክር አካሂደዋል።

የአትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ በተለያዩ ባለሀብቶች እየተሰሩ ያሉ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ እና በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን መግለጹን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም