የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2015 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ከአሜሪካ ግምጃ ቤት ምክትል ረዳት ፀሐፊ ኤሪክ ሜየር ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር ላይ ያተኮረ መሆኑን ባንኩ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው መረጃ አመልክቷል።
የባንኩ ገዥ የአሜሪካ ግምጃ ቤት በኢትዮጵያ እድገትን ለማፈጠን እና የኢኮኖሚ መረጋጋት እንዲመጣ እየተወጣ ላለው ገንቢ ሚና ምስጋናቸውን አቅርበዋል።