የሕንድ-አፍሪካ አይ ሲ ቲ ኤክስፖ በነሐሴ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
የሕንድ-አፍሪካ አይ ሲ ቲ ኤክስፖ በነሐሴ ወር በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/2015 (ኢዜአ):-የሕንድ-አፍሪካ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ(አይ ሲ ቲ) ኤክስፖ ነሐሴ 3 እና 4/2015 በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል እንደሚካሄድ ተገለጸ።
በሕንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ የኤክስፖው አዘጋጅ ከሆነው ‘Telecom Equipment and Services Export Promotion Council’ ዳይሬክተር አሩን ጉፕታ ጋር ዝግጅቱን አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል።
በኤክስፖው ከ60 በላይ የሕንድ፣ የኢትዮጵያ እና ሌሎች የአፍሪካ አገራት የአይ ሲ ቲ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በአይ ሲ ቲው ዘርፍ ሕንድ እና አፍሪካ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር የኤክስፖው አላማ መሆኑም ተገልጿል።