በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኩባንያዎች በወርቅ፣ ቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኩባንያዎች በወርቅ፣ ቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24/2015 (ኢዜአ):- በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ ኩባንያዎች በወርቅ፣ ቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት ዘርፍ ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ።
በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ በማዕድን ዘርፍ ከተሰማሩ የመታብ አልነምር (ማዕድን አውጪ) እና የአያድ አል አቶቢ ኩባንያዎች ባለቤት እና ኃላፊዎችን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
አምባሳደር ሌንጮ በኢትዮጵያ ስላለው ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጭ፣ በአገሪቷ በስፋት ስለሚገኘው የፖታሽ፣ የወርቅና የተለያዩ ማዕድናት ክምችት አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ኩባንያዎቹ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል።
ኩባንያዎቹ ለተደረገላቸው አቀባበልና ገለጻ ያመሰገኑ ሲሆን፥ በወርቅ፣ በቴክኖሎጂና ማዳበሪያ ማምረት ዘርፍ ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።
በቅርቡ በኢትዮጵያ ተገኝተው በመስኮቹ ላይ ጥናት በማድረግ ኢንቨስት እንደሚያደረጉ ቃል መግባታቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።